በሚያምሩ ልጣፎች እና የላቁ ባህሪያት አማካኝነት ከማሳያዎ ምርጡን ያግኙ። ከራስዎ ፎቶዎች ውስጥ፣ ከGoogle Earth ስብስብ ውስጥ አንድ ፎቶ፣ ከGoogle+ አንድ የመሬት ገጽታ እና ተጨማሪ አንድ ይምረጡ። ለፈለጉት ያህል ጊዜ ይቀይሩ፣ ስለዚህ ስልክዎ ሁልጊዜ የእርስዎን ቅጥ ይወክላል። 
 • እያደገ መሄዱን በሚቀጥል ስብስብ ይደሰቱ። ምስሎችን ከGoogle Earth፣ Google+ እና ሌሎች አጋሮች ይድረሱ። 
 • መዝናኛዎን በእጥፍ ያሳድጉት። በማያ ገጽ ቁልፍዎ ላይ አንድ ልጣፍ ለዓለም ያሳዩ፣ እና ለራስዎ በመነሻ ማያ ገጽዎ ላይ አንድ ያስቀምጡ። (Android™ 7.0፣ Nougat እና ከዚያ በላይ ያስፈልጋል።) 
 • እያንዳንዱን ቀን እንደ አዲስ ይጀምሩት። የሚወዱትን ምድብ ይምረጡና በየቀኑ አዲስ የልጣፍ ምስል ያገኛሉ። 
 የፈቃዶች ማስታወቂያ 
 ፎቶዎች/ሚዲያ/ፋይሎች፦ እርስዎ ብጁ ፎቶዎችን እንደ ልጣፍ መጠቀም እንዲችሉ ያስፈልጋል። 
 ማከማቻ፦ አሁን የተዘጋጀውን ልጣፍ እንዲያሳይ እና እርስዎ ብጁ ፎቶዎችን እንደ ልጣፍ መጠቀም እንዲችሉ ያስፈልጋል።